የድህረወሊድ እንክብካቤ (postnatal care)

We are excited to announce that our mixed-method study on the factors affecting postnatal care service utilization has been published in PLOS ONE

Although the journey from conducting the study to its publication was somewhat lengthy, the issue addressed remains highly relevant, as Nepal continues to face challenges in increasing postnatal care service coverage as per protocol.

Huge thanks to everyone who contributed to this study!

👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👦👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧👨‍👧

አንድ ሴት ከወለደች በኋላ ሊደረግላት የሚገቡ ሙያዊ እገዛ ፣ ምክር እና  አስተምሮ የድህረ ወሊድ እንክብካቤ እንለዋለን።
ይህም ከወለደችበት ደቂቃ አንስቶ እስከ አርባ አምስተኛ ቀን ድረስ የሚደርስ ሲሆን እንደ እርግዝና ጊዜ ሁሉ ለእናት ጤና አስጊ የሆኑ ችግሮች ጎልተው የሚታዩበት ወቅት ስለሆነ እና
ለተወለደው ጨቅላም የተለዪ አደገኛ ሁኔታዎች ሊከሰቱ ስለሚችል ክትትል እና እንክብካቤ ማድረግ ብልህነት ነው።

ውስብስብ ችግሮቹ ምንድናቸው?
በዚህ ወቅት የሚፈጠሩ ቸግሮች በርግዝና ጊዜ የነበሩ አልያም አዲስ የተፈጠሩ ሊሆኑ ይችላሉ። ከእነዚህም መካከል

  • የማህፀን ኢንፌክሽን
  • ደም መፍሰስ
  • ግፊትና ማንቀጥቀጥ
  • የጡት ህመም
  • የቁስል መፈታት
  • ፊስቱላ
  • የሳንባ ምች
  • የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
  • ኪንታሮት
  • የደም መርጋት

አደገኛ ምልክቶች ምንድናቸው?
በእናት ወይም በልጅ ላይ የሚከሰቱ ዋናዋና የጤና ችግሮች ሲታዩ ያለምንም ቅድመሁኔታ ወደ ወለድሽበት  ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ማድረግ ያሻል።

የእናት አደገኛ ምልክቶች

  1. ትኩሳት
  2. ከፍተኛ ራስ ምታት እና የአይን ብዥታ
  3. የሰውነት አብጠት
  4. የሽንት ወይም ሰገራ አለመቆጣጠር
  5. ራስ መሳት
  6. የጡት እብጠትና ህመም
  7. ሳል እና አየር ማጠር
  8. ሽታ የለው ፈሳሽ በማህፀን መኖር

የልጅ አደገኛ ምልክቶች

  1. የፈጠነ አተነፋፈስ
  2. ጡት አለመጥባት
  3. የማያቋርጥ ለቅሶ
  4. ትኩሳት
  5. የሰውነት ቢጫ መሆን
  6. የሽንትና ሰገራ አለመውጣት
    . 👇👇👇👇👇👇👇
    ይቀጥላል
    በድህረ ወሊድ ወቅት የሚጠቅሙ
    ተጨማሪ ምክሮች

አመጋገብ

ከወሊድ በኋላ ገንቢ እና ጠጋኝ ምግቦችን መመገብ የተለመደ እና የሚበረታታ ጉዳይ ሲሆን አትክልት እና ፍራፍሬ ጨምሮ ጤነኛ አመጋገብ ማዘውተር ተገቢ ነው።
ቅባት፣ ጮማ፣ጨውና ቅመማቅመም ማብዛት ለጤና መታወክ ስለሚያጋልጥ መጠንቀቅ ያሻል።
በኦፕራሲዮን ከወለደች በአንዳንድ ማህበረሰብ ስጋ እና የወተት ተዋፅዖ መውሰድ ቁስል እንዳይድን እንዲያመረቅዝ ያደርጋል የሚል የተሳሳተ አስተሳሰብ ስለሆነ ኦፕራሲዮን ያደረገሽን ሃኪም በፅሞና መከታተል ወይም መጠየቅ ተገቢ ነው።

ቀጠሮ

ከወለድሽ በኋላ ክትትሉ ስለሚቀጥል በ7ኛ ቀን እና በ45 ቀን አንቺ እና ልጅሽ በወለድሽበት ጤና ተቋም መታየት መልካም ነው።

እንቅስቃሴ

በብዙ ማህበረሰብ አራስ ቤት ውስጥ እንድትወሰን እነዳትንቀሳቀስ ጓዳ ውስጥ እንድትሆንና ተከልላ እንድትቀመጥ የሚደረጉ ሲሆን የማይበረታታ እና ያረጀ ፋሽን ስለሆነ ቤት ውስጥ መጠነኛ መደበኛ እንቅስቃሴ እንድታደርግ አየር እና የፀሃይ ብርሃን እንድታገኝ ያስፈልጋል።
ባለመንቀሳቀስ ምክንያት የደም መርጋት ፣ ኢንፌክሽን፣ የሆድ ድርቀት እና የአጥንት መሳሳት ሊከሰት ይችላል።
አራሷ በሚመቻት መጠንና ሰዓት እንድትንቀሳቀስ ማበረታታት ያስፈልጋል።

የአካል ንፅህና

በማህፀን የወለደች እናት በወለደችበት ቀን ገላዋን መታጠብ የምትችል ሲሆን በደንገጡር ታግዛ ካልሆነም ተቀምጣ እንድትታጠብ ይመከራል።
በኦፕራሲዮን ከወለደች ደግሞ ከ72 ሰዓት በኃላ መታጠብ እንደሚቻል ሳይንስ ያስቀምጣል።

የመራቢያ አካላት ንፅህና

የመራቢያ አካል ላይ የተደረገ መለስተኛ ቀዶጥገና ካለ በቀን 4-6 ጊዜ ለብ ባለውሃ ለ10ቀናት ያህል መታጠብ ያስፈልጋል።
ጨው እና ዲቶል እንዲሁም ሌሎች በሃኪም ያልታዘዙ ባዕድ ነገሮች መጨመር ወይም መቀባት ለኢንፌክሽንና ለቁስል መፈታት ስለሚያጋልጥ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

የረካቤ ስጋ

ከወሊድ በኋላ የመራቢያ አካላት ቁስለት ብግነት እና እብጠት ከዳነ አና አንቺ የግንኙነት ፍላጎት ካለሽ ግንኙነት አይከለከልም። ይህም ከ4-6ሳምንት በኋላ እንደሆነ ሳይንስ ቢያስቀምጥም በተለያየ ቤተ እምነቶች ከ45ቀናት በኋላ እንደሚፈቀድ ተቀምጣሉ።

የወሊድ መከላከያ

አንድ ሴት ከወለደች በኋላ ከ45ቀናት ጀምሮ እርግዝና ሊከሰት ይችላል። ምንም እንኳን የወርአበባ ባይመጣም ጡት ብቻ የምታጠባም ቢሆን መቶበመቶ እርግዝና ሊከላከል ስለማይችል አስቀድሞ መጠንቀቅ ግድ ነው።

የልጅ ክትባት

ከወለድሽ በኋላ ወዳውኑ የሚሰጡ ክትባቶች ልጅሽ ማግኘቱ ካረጋገጥሽ በኋላ የቀጣይ ቀጠሮ ይዘሸ መሄድን አትርሺ
ልጅሽ እንደተወለደ ፣ 45 ቀኑ ፣ በ10 ሳምንቱ ፣ በ14 ሳምንቱ፣ በ6 ወሩ እንዲሁም በ9 ወሩ ክትባት መውሰድ እንዳለበት አስታውሺ
ክትባቶቹ ከፖሊዮ፣ ከኩፍኝ ፣ከቲቢ ፣ ከተቅማጥ ፣ ከሳንባምች ፣ ከቴታነስ ፣ ከጉበት ቫይረስ ፣ ከማጅራት ገትር ፣ ከትክትክ እና ሌሎች አደገኛ ህመሞች እንደሚከላከል አስቢ።

የልጅ እጥበት

ያለጊዜው የተወለደ ልጅ ከሆነ ማጠብ ሙቀት ከሰውነቱ እንዲባክን ስለሚያደርግ በቂ ኪሎ እስከሚያገኝ በዋይፕስ መጥረግ ይቻላል። በጊዜው የተወለደ ለልጅ ከሆነ ግን ከተወለደ 24 ሰዓታት በኋላ ሞቅ ባለ ቤት ውስጥ ለብ ባለ ውሃ አጥቦ በንፁህ ጨርቅ በማድረቅ አቅፎ ማሞቅ ያስፈልጋል።

የጡት ማጥባትና የልጅ አመጋገብ

ከተወለደ ደቂቃ እስከ 6ወራት የእናት ጡት ብቻ መስጠት ለልጁ ጤንነትና ተመጣጣኝ እድገት ወሳኝ ሚና አለው። ውሃ መስጠት ፣ ቂቤ ማላስ እንዲሁም ስኳር በጥብጦ ማጠጣት የመይደገፉ ኋላቀር አሰራሮች መሆናቸው አውቀሽ ለ6 ወራት ጡት ብቻ መጥባትን ልማድ እናድርግ።

ፀሃይ ማሞቅ

ከወለድሽ 7-10ቀናት ጀምሮ ልጅሽን የፀሃይ ብርሃን በየቀኑ ማሳየት ያስፈልጋል። ልጅሽን ምንም ሳትቀቢ የጠዋት ፀሃይ 30-40ደቂቃ ማሞቅ እድገቱ የተስተካከለ እና አጥንቱ የጠነከረ እንዲሆን ያደርጋል።

ማጠቃለያ፦  ሳይንሳዊ ዳራ ከሌላቸው አጉል አስተሳሰቦች ተላቀን የነቃና ጤነኛ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁላችንም የድርሻችን እንወጣ።
Dr. Kool

https://ethiogoogle.com

2 thoughts on “የድህረወሊድ እንክብካቤ (postnatal care)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *